DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 18, 2025 at 02:59 PM
የሥርጭት ማስታወቂያ ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ አድማጮች እንደምን አላችሁ? በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 1 ሰዓት ላይ የሚጀምረው የዛሬው ሥርጭታችን እንደተለመደው የዓለማችን ዓበይት ዜናዎችን በማቅረብ ይጀምራል። ዜናውን ተከትሎ በሚቀርበው የዜና መፅሔታችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከሐገሪቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያካሄዱት ውይይት፤ መንግስት በየዕለቱ ከባንክ የሚወጣውን የገንዘብ መጠን መገደቡን፤ በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ፤ ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል የሚኖሩ ተፈናቃዮች ስሞታ የሚሉ ርዕሶች ተካተዋል። ሳምንታዊ ዝግጅቶች ከኢኮኖሚው ዓለምና ሳይንስና ቴክኖሎጂም ሰዓታቸውን ጠብቀው ይቀርባሉ። አብራችሁን እንድትሆኑ ከወዲሁ በአክብሮት እንጋብዛለን።
Image from DW Amharic: የሥርጭት ማስታወቂያ ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ አድማጮች እንደምን አላችሁ? በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 1 ሰ...

Comments