
DW Amharic
June 18, 2025 at 05:06 PM
የሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መንግሥት ወደየቀያቸው እንዲመልሳቸው ጠየቁ። በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞን በ15 መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት ተፈናቃዮች ሰብአዊ እርዳታ እያገኙ ስላልሆነ መንግሥት ሰላም አስከብሮ ወደመጡበት ይመልሰን እያሉ ነው። ትግራይ ውስጥ ጦርነት ያፈናቀላቸው ወገኖች በበኩላቸው መንግሥት ምላሽ ካልሰጣቸው እራሳቸው እርምጃ እንደሚወስዱ አሳስበዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ዜጎቻቸው ላይ የጉዞ እገዳ እንዳይጣል ተገቢውን ማጣሪያ እንዲያደርጉ ለ36 ሃገራት ማሳሰቢያ ሰጠ። ማሳሰቢያው ከደረሳቸው 25ቱ የአፍሪቃ ሃገራት ሲሆኑ ኢትዮጵያ አንዷ ናት።
እስራኤል ሁለት የኢራን የኒኩሊየር ማብላያ የሚገኝባቸው ሕንጻዎች አወደመች። ኢራን በአሜሪካ ድጋፍ ተደርጓል ላለችው ጥቃት የምትመልሰው አጸፋ የከፋ እንዲሚሆን ዝታለች። እስራኤል ለጥቃቱ ከ50 በላይ ተዋጊ ጀቶችን ማሰለፏን አስታውቃለች ።
https://shorturl.at/BwGWq
❤️
1