
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
June 14, 2025 at 10:20 AM
"ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ሁለት ፉርጎ ይዞ በሠዓት 20 ኪሎ ሜትር ያደርግ የነበረው ጉዞ 'ነበረ' ሆኗል ክቡር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
ከኢትዮ - ጅቡቲ ባቡር ከለውጡ በፊት ሳይሆን ከለውጡ በኋላ እስከዛሬ አራት ዓመት ድረስ ሁለት ፉርጎ ይዞ በሠዓት 20 ኪሎ ሜትር ይጓዝ እንደነበረና ይህ ታሪክ ተለውጦ 'ነበር' ሆኗል ሲሉ ክቡር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
አሁን ላይ ባቡሩን በመሠረታዊ ደረጃ ለመቀየር በተሰሩ ስራዎች በሠዓት 60 ኪሎ ሜትር እንዲጓዝ ማድረግ መቻሉን አክለዋለ።
ፍጥነት ከመጨመር ባሻገር በርካታ ፉርጎዎችን የማመላለስ አቅም ላይ ደርሷል።
ይህ አቅም መፈጠሩ ጅምር መሆኑን በማስታወስ ከዚህ በላይ ማደግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።