Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
June 16, 2025 at 02:12 PM
ዛሬ ከሜዲትራኒያን የባህር ማጓጓዣ ኩባንያ (ኤም.ኤስ.ሲ) ጋር በመተባበር 104 ባዶ 20 ጫማ ኮንቴይነሮችን በተሳካ ሁኔታ ከጅቡቲ ወደ እንዶዴ የጭነት ማዕከል በማስገባት የኢትዮጵያን የወጪ ኢኮኖሚ ለማሳለጥ ተዘጋጅተናል! እነዚህ ኮንቴነሮች በቅርቡ ለፕሪሚየም ደንበኞች ያመቻቸነውን የክሬዲት አገልግሎት በመደገፍ እንደ ቡና፣ የቅባት እህሎች እና ሌሎች የወጪ ንግድ ምርቶችን ለማጓጓዝ በእጅጉ ያገለግላሉ። ይህም የሀገር ውስጥ ላኪዎች ምርቶቻቸውን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲያደርሱ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋለ። ይሄ ገና ጅምር ነው—የወጪ ንግዳችንን በተቃና ሁኔታ ለማላቅ የምናደርገውን ብርቱ ጥረት በመቀጠል ተጨማሪ ተግባራትን አጠንክረን እንቀጥላለን። ይህንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን የሎጂስቲክስ ስራ እንከን የለሽ እና ቀልጣፋ ያደረጋችሁ ቁርጠኛ ሠራተኞቻችን፣ ለኤምኤስሲ አጋሮቻችን እና ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን እናመሰግናለን።
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): ዛሬ ከሜዲትራኒያን የባህር ማጓጓዣ ኩባንያ (ኤም.ኤስ.ሲ) ጋር በመተባበር 104 ባዶ 20 ጫማ ኮንቴይነሮችን በ...

Comments