Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
June 17, 2025 at 07:55 AM
የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት - ከመደበኛ እስከ ቻርተርድ !! ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ከመደበኛ የባቡር ጉዞዎች በተጨማሪ ከደንበኞች በትዕዛዝ የሚቀርቡ ልዩ ጉዞዎችን ማቅረብ መጀመሩን  ይፋ አድርጓል። በኦንላይን የጉዞ ትኬት በመቁረጥ ከሚደረገው መደበኛ  የባቡር ጉዞ በተጨማሪ በምቾት፣ ፈጣን እና አስደሳች የቻርተርድ ባቡር ጉዞ መጀመሩን ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልፀዋል። የቻርተርድ አገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ ሰብሰብ ብለው አስደሳች ጉዞ ለማድረግ፣ የተለያዩ ሁነቶችን አስመልክቶ ለሚደረግ ጉዞ ወይም ድርጅቶች በተለየ መልኩ ለሚያደርጓቸው ዝግጅት በልዩ መልኩ የሚደረግ አስደሳች ጉዞ መሆኑን ጠቁመዋል። ከለቡ እስከ ድሬዳዋ  የሀገርዎን መልክአ ምድርና ተፈጥሮን እያደነቁ እንዲጓዙ፤ ጉዞዎን እስከ ጅቡቲ ለማድረግ ካቀዱም በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎቱ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የሚያደርጉት ጉዞ አስተማማኝ እና ምቹ ፤ ተወዳዳሪ እና ተመጣጣኝ ዋጋ የሚጠየቅበት ልዩ የባቡር ውስጥ መስተንግዶን ያካተተ  መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ገልፀዋል።
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት - ከመደበኛ እስከ ቻርተርድ !!  ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ከመደበኛ የባቡር ጉዞዎች ...

Comments