
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
June 19, 2025 at 08:06 AM
አስቸኳይ ማስታወቂያ!
ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር በወጪ ገቢ ንግድ ላይ የተሰማሩ ደንበኞች በሚገጥማቸው የኮንቴነር እጥረት ምክንያት እንቅስቃሴያቸው እንዳይስተጓጎል በማሰብ በቂ ኮንቴነር አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ደንበኞች ለወጪ ንግድ የሚውሉ ባዶ ኮንቴነሮችን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ይሁንና አንዳንድ ደንበኞች ባዶ ኮንቴነሮችን ለመውሰድ ለተቋማችን ጥያቄ ካቀረቡ በኃላ በተገቢው ጊዜ የጠየቁትን ኮንቴር ማንሳት አልቻሉም፡፡ ይህም በጭነት ጣቢያዎች ላይ አላስፈላጊ መጨናነቅ እንዲፈጠር፣ የኤክስፖርት እንቅስቃሴ በተያዘለት ጊዜ እንዳከናወን በማድረግ በሎጂስቲክስ ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በተለይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የቡና እና እህል ላኪ ደንበኞች ባዶ ኮንቴነር ካዘዙ በኋላ በተመደበላቸው ጊዜ ማንሳት አልቻሉም፡፡
1. AMG……30 ኮንቴነሮች
2. Testi…… 20 ኮንቴነሮች
3. Kebir…... 20 ኮንቴነሮች
4. Ethio Agri…….10 ኮንቴነሮች
5. Tracon ………... 20 ኮንቴነሮች
በመሆኑም ኮንቴነሮቹን በአስቸኳይ እንድታነሱ እየጠየቅን በጊዜ ማንሳት የማትችሉ ከሆነ ግን በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ለሚገኙ ደንበኞች የምናስተላልፍ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ እባክዎ የግሎባል ሎጂስቲክስ የስራ ክፍልን ያነጋግሩ፡፡ ወይም 9546 ይደውሉ፡፡
ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ
