
Addis Ababa Education Bureau
June 1, 2025 at 05:58 AM
በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ወረገኑ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመማር ማስተማር ስራዉ ምቹ እንዲሆን ለማድረግ ተችላል፡፡
(ግንቦት 24/2017 ዓ.ም) በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 የሚገኘው ወረገኑ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉለት በማድረግ ለመማር ማስተማር ስራዉ ምቹ እንዲሆን ተደርጋል፡፡
ማህበረሰቡ ሲያነሳው የነበረዉን የረዥም ጊዜ ጥያቄ መሰረት በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት በመስራቱ በትምህርት ቤቱ አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች የጂ+4 ህንፃ ፣ የአስተዳደር ህንፃ እና የመጸዳጃ ቤቶች ተገንብተው እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ለረዥም ጊዜ ችግር ሆኖ የቆየውን የውሃ እጥረት ለመፍታት የከርሰ ምድር ውሃ የማጎልበት ሥራ በመስራት ለአገልግሎት እንዲዉል ተደርጋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

👍
1