
Addis Ababa Education Bureau
June 2, 2025 at 07:23 AM
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(ግንቦት 25/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል" አገልጋይ መሪነት " በሚል ርዕስ የአገልጋይ መሪ ምንነትና ባህሪያትን መሰረት ያደረገ ሰነድ አቅርበዋል ::
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ትክክለኛ የአገልግሎት ስልቶችን በመረዳት እንደቢሮው ባህሪ የትምህርት ጉዳይን ጠንቅቆ በማወቅ ስራን የማስፈፀም አቅምን ማሳደግ እንዲሁም ባገኙት እውቀት መነሻነት ለመምራትና ለማገልገል ቁርጠኛ የሆነ ማንነት ከሁሉም አመራር ፣ ፈጻሚ ፣ ቡድን መሪና ዳይሬክተሮች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል ::
የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለማግኘት
https://linktr.ee/aacaebc
