Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 2, 2025 at 10:07 AM
የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ:: (ግንቦት 25/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከምገባ አጄንሲ ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልእክት በ2018 ዓ.ም 1.2 ሚሊየን ለሚሆኑ ተማሪዎች ደንብ ልብስ ለመስጠት በከተማ አስተዳደሩ እቅድ መያዙን ገልፀው ስልጠናው በ2017 ዓ.ም የታዩ እጥረቶችን ለማረም በጥንካሬ የታዩትን አጠናክሮ ለመቀጠልና ተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል:: አቶ ሳምሶን አክለውም የደንብ ልብሱ በአግባቡ ካልተሰራ ተማሪዎች የደንብ ልብስ እንዲያጡ ብሎም የመንግስት ሀብት እንዲባክን የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት የስልጠናው ተሳታፊዎች ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ አቅርቦት እንዲኖር በኃላፊነትና በባለቤትነት ስሜት የጥራት ቁጥጥሩን እንዲያደርጉ አሳስበዋል:: የምገባ ኤጀንሲ ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር አቶ ቢንያም በበኩላቸው በስልጠናው የተነሱ ሃሳቦችን በመውሰድ የተሻለ ጥራት ያለው የደንብ ልብስ ለማሰራጨት ኤጀንሲው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀው የጥራት ኮሚቴው የጥራት ችግር እንዳያጋጥም ልብሱን ሲረከቡ ጥራቱን በትኩረት በማረጋገጥ እንዲሆን አሳስበዋል:: በስልጠናው ላይ የደንብ ልብስ ጥራት ለማረጋገጥ የሚረዱ ነጥቦች የያዘ ሰነድ የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ አቶ ዳግም አለማየሁ እና የጎፋ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ቴክስታይል አሰልጣኝ አቶ ኃይልዬ ዘውዱ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤት መሻሻል ምክትል ርዕሳነ መምህራን: የክፍለከተማና ወረዳ ተ. ወ. ማ ተወካዮች እና የተማሪ ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር ኮሚቴ ተወካዮች ተሳትፈዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ::  (ግንቦት 2...
👍 1

Comments