Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 3, 2025 at 05:57 AM
ከተማ አቀፉን የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመደገፍና ተገቢውን ክትትል ለማድረግ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ውይይት አካሄደ። (ግንቦት 26/2017 ዓ.ም) የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን፣ የመምህራን ማህበር አመራሮችን ጨምሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች የተውጣጡ አመራሮች የተካተቱበት አደረጃጀት ሲሆን በውይይቱ የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ከዚህ በፊት በከተማ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ዘንድሮ የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተያዘለት መርሀግብር መሰረት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚቋቋሙ የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቶች ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት የተለመደ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መውጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቱ የፈተና ማስፈጸሚያ እቅድ በማውጣት በየደረጃው የንቅናቄ መድረኮች መዘጋጀታቸውን የማረጋገጥ ፣የፈተና ስርጭትና ርክክቡ በጥብቅ ዲሲፒሊን መመራቱን ፣ፈተናው ወደ ፈተና ጣቢያዎች ሲሰራጭ በጉዞ ሂደትም ሆነ በሚቆዩባቸው ቦታዎች ደህንነታቸው መጠበቁን የማረጋገጥ እንዲሁም የፈተና አስፈጻሚዎች በመመሪያው መሰረት በጥንቃቄ እንዲመለመሉ ድጋፍ የማድረግን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ኃላፊነቶች የሚጠበቅበት መሆኑን አመላክተዋል። ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ194 የፈተና ጣቢያዎች ለ71,972 ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 4 የሚሰጥ ሲሆን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናው ደግሞ በ192 የፈተና ጣቢያዎች ለ 80,323 ተማሪዎች ሰኔ 10፣11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በውይይቱ ተገልጿል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: ከተማ አቀፉን የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመደገፍና ተገቢውን ክትትል ለማ...

Comments