Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 3, 2025 at 02:45 PM
“ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ሃሳብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ (ግንቦት 26/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ሃሳብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች በተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ ላይ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት ተካሄዳል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልእክት መንግስት የሲቪል ሰርቫንቱን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ለህብረተሰቡ ለማድረስ በርካታ ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ውይይቱ በሲቪል ሰርቫንቱ መካከል ሀገራዊ አንድነት ለማጠናከርና በሀገራችን እድገት ላይ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት በማቀራረብ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የራሱ በጎ ተፅዕኖ እንደሚኖረው አስረድተዋል :: ሀላፊው አክለዉም የውይይቱ ተሳታፊዎች በሀገራዊ መግባባት ላይ የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ሚና እንዳለው በማሰብ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ በነፃነትና በንቃት መሳተፋቸዉን ገልጸዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር መድረኩ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎቱ በለውጡ ሥራ ምን ተግባር ነበረው የሚለው ሀሳብ ላይ ግልፀኝነት እንደሚፈጥር አብራርተው በሀገራዊ ጉዳይ ላይም በቂ መረጃ እንዲኖረው ያደርጋል ብለዋል :: የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ሰነዱ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሰራተኞች በቂ መረጃ እንዲኖራቸዉ ከማድረግም ባሻገር ብቃት ያለው ሰራተኛ ለሀገር ብልፅግና መረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ሰራተኞች ተረድተው ለዚህ መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል። በመጨረሻም በቀጣይ በከተማ አስተዳደሩና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄድ ውይይቶች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች ምርጫ ተካሂዷል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: “ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ሃሳብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት...

Comments