Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 7, 2025 at 07:49 PM
ኦዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ግንቦት 30/2017 ዓ.ም) ትምህርት ለሀገራዊ ዕድገትና ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ የሚጫወተው ሚና እጅግ የላቀ ነው፡፡ ከሀገራዊው ለውጥ ማግሥት መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የትምህርት መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሚገኘው ኦዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአካባቢው ለረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አለመኖር ጥያቄ ለመመለስ በአስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶች የተገነባ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ እንዲሆን ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችና የአስተዳደር ሕንፃ በትምህርት ቤቱ የተገነባ ሲሆን ፣ የመማር ማስተማር ሂደቱ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆንም ግብዓቶችን የማሟላት ሥራዎችም ተከናውነዋል፡፡ የኦዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአካባቢው ማኅበረሰብ የትምህርት አገልግሎት በመስጠትና በክፍለ ከተማው የመማር ማስተማር ሂደቱን በማሳለጥ ለትምህርት ጥራት ማደግ ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለማግኘት https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: ኦዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት                    (ግንቦት 30/2017 ዓ.ም) ትምህርት ለሀገራዊ...

Comments