
Addis Ababa Education Bureau
June 9, 2025 at 08:15 AM
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(ሰኔ 2/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የትምህርት ግብዓት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሀነመስቀል የግልፅ አላማ ምንነትና አላማ መቅረፅ በሚል ርዕስ ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ አቅርበዋል ::
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ግልፅ አላማ ማስቀመጥና ለአላማው መሰካት መጣር እንደሚገባ ጠቅሰው ለአላማ መሳካት አዕምሮን ዝግጁ ከማድረግና ከማሳመን ባለፈ ለአዕምሮ መልካም ነገርን መመገብ መሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም ልጆች ውጤታማ እንዲሆኑ አቅም እንዳላቸው ፤ ማድረግ እንደሚችሉ እንዲሁም በራሳቸው አቅም እምነት እንዲኖራቸዉ አዕምሮዋቸዉን በዚህ አስተሳሰብ እንዲገራ ካደረግን ውጤታማ ትውልድ ለመፍጠር እንችላለን ብለዋል፡፡
ለአላማ መሳካት መልካም ነገርን ማሰብ ለስኬታማነት ቁልፍ መሆኑን ያነሱት ሀላፊው ሰው መልካም ነገርን ማሰብና ለዚህ መሳካት ደግሞ መስራት ከቻለ ህልሙን ለማሳካት ይችላል ብለዋል፡፡ ለአላማ መሰካት በጋራ መስራትም ትልቅ ቦታ ላይ እንደሚያደርስ ገልጸዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
