Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 9, 2025 at 01:57 PM
የመምህራንን የ25/75 የማህበር ቤት ግንባታን ወደ ተግባር ለማስገባት እንዲቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ። (ሰኔ 2 /2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ ከንቲባ ፅ/ቤት ፤ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፤ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ፤ የህብረት ስራ ማህበር ፤ የመንገዶች ባለስልጣን ፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፣ የመምህራን ማህበር ተወካዮች እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የመምህራንን የ25/75 የማህበር ቤት ግንባታን ወደ ተግባር ለማስገባት እንዲቻል ውይይት ተካሄዳል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በዚህ የስራ ሂደት ውስጥ የተደራጁና ወደ ተግባር ለመግባት የሚችሉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል መምህራን መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በንግድ ባንክ ከተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት በኋላም ከመምህራን ጋር በተደረገ ውይይት የተደራጁ መምህራን ዝግጁነታቸውን አሳውቀዋል ብለዋል። ሀላፊው አክለዉም ውይይቱ በዚህ ስራ ሂደት ውስጥ የሚካተቱ ባለድርሻ አካላት የሚመከለታቸዉን ተግባር በመውስድ ወደ ተግባር ለመግባት ያግዘናል ብለዋል። የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ለመምህራን ቅድሚያ የተሰጠው የ25/ 75 የማህበር ቤት ግንባታን ወደ ተግባር ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በእቅዶች ላይ በመናበብ በአንድ ለመጓዝ እንዳያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ውይይት ነው ያሉ ሲሆን ወደ ተግባር ለመግባት እና የስራ ድርሻ ለመከፋፈል እንዲሁም ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን ለመነጋገር ታላሚ ያደረገ ውይይት ነው ብለዋል። መምህራንን በህብረት ስራ አደራጅቶ ለማስጀመር የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ በቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በኩል የቀረበ ሲሆን በዝግጅት ምእራፍ ከባንክ ጋር ብድር በአነስተኛ ወለድ ምጣኔ ስምምነት መደረጉ ፤ ከ23 ሺ በላይ መምህራን በህብረት ስራ ማህበር እንዲደራጁ መደረጉ ፤ እንዲሁም ከሁሉም የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላትም በቀጣይ የሚጠበቁ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በመጨረሻም ለስራው ስኬታማነት አብይ እና ቴክኒካል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን በየጊዜውም መድረክ እየተፈጠረ እና የስራው ሂደት እየተገመገመ የሚሄድ መሆኑ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶበታል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: የመምህራንን የ25/75 የማህበር ቤት ግንባታን ወደ ተግባር ለማስገባት እንዲቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት...
😂 1

Comments