Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 10, 2025 at 07:50 AM
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምራል። (ሰኔ 3/2017 ዓ.ም) በክፍለ ከተማው በዛሬው እለት መሰጠት የጀመረው የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በ17 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከ3400 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። ፈተናውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ አስታጥቄ አስጀምረውታል። ተማሪዎች በጠዋቱ ፈረቃ አማርኛ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎችን የሚወስዱ ሲሆኑ ሌሎች ትምህርቶችንም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለ2 ቀናት የሚወስዱ ይሆናል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም  የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምራ...

Comments