Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 12, 2025 at 09:14 AM
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በትምህርት ቢሮ ልምድ ልውውጥ አካሄዱ። (ሰኔ 5/2017 ዓ.ም) የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብሩ በዋናነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ በሚያካሂደው የዕውቀት ሽግግር መርሀግብር ውጤታማ የሆነበትን አሰራር ልምድ ለመቅሰም ታስቦ መዘጋጀቱን ከቢሮው የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያ ሳያል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን አመራሮች በተቋሙ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ በመምጣታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ምስጋና አቅርበው ትምህርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ ማለዳ በሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የማስፈጸሚያ እቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ ወቅታዊ የሆኑና የሰራተኛውን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ ርዕሶች እየተመረጡ በመቅረባቸው በተቋም ባህል ግንባታ እና በሰራተኛው የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይ አወንታዊ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆኑን አመላክተዋል። በቢሮ የሚካሄደው የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መድረክ ያበረከተው አስተዋጽኦ በየሩብ አመቱ ከመገምገሙ ባሻገር የተቋም ባህል ግንባታን በማረጋገጥ ሂደት ያመጣው ውጤት የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት እየተካሄደ ግብረመልሱ ለሚመለከታቸው አካላት እየተላከ የሚገመገም መሆኑን የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ አስታውቀዋል። ልምድ ልውውጡን ለማካሄድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ ሳያቆራረጥ እያካሄደው የሚገኘው የዕውቀት ሽግግር መርሀግብር የቢሮው አመራሮች በፕሮግራሙ ከመሳተፍ ጀምሮ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረጋቸው ውጤታማ መሆኑን በልምድ ልውውጡ በቀረበላቸው መረጃዎች ማረጋገጣቸውን በመግለጽ በቀጣይ ያገኙትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ በተቋማቸው ተግባራዊ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል። ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ ከተማ ግዢና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም ከጉለሌ እጽዋት ማዕከል የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ተመሳሳይ ልምድ መውሰዳቸው ተገልጿል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በትምህርት ቢሮ ልምድ ልውው...

Comments