
Addis Ababa Education Bureau
June 16, 2025 at 07:28 AM
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(ሰኔ 9/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የመምህራን ማህበር ፣ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወ/ኪዳን በ7/24 የትምህርት መረጃ አስተዳደር ፖርታል አጠቃላይ አተገባበርና አጠቃቀም ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ መክፈቻ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ መረጃ ለትምህርት ስራ ውጤታማነት በተለይም ትክክለኛ ውሳኔን ለማስተላለፍ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን ጠቅሰው 7/24 የትምህርት መረጃ አስተዳደር ፖርታል የከተማ አስተዳደሩን የትምህርት መረጃዎችን ከአንድ ቋት ለማግኘት እንዲሁም ከትምህርት ቤት እስከ ቢሮ ድረስ ያሉ መረጃዎች ወጥ እንዲሆኑ ያስችላል ያሉ ሲሆን ፖርታሉ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመደረኩ ማጠቃለያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ መረጃ ለትምህርት ስራ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ገልጸው የተጀመረውን ስራ በማሳለጥ አንድ አይነት መረጃ ከአንድ ቋት መስጠት እንዲቻል በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
