Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 16, 2025 at 01:37 PM
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ (ሰኔ 9/2017 ዓ.ም) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስተር በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ተማሪዎች ከፈተና ስርቆትና ኩረጃ በመውጣት አጥንቼ አውቄ ፈተናውን ማለፍ አለብኝ የሚል አስተሳሰብ ያለው ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ መፍጠር አለብን ሲሉ ተናግረዋል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከመከላከያ ሠራዊት እና ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ለአራት ዓመታት የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ እና ተማሪዎች የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል። ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ቀደም ባሉት ጊዜያት በስርቆትና በኩረጃ ይታወቅ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ የለውጡ መንግስታችን በወሰደው ቁርጠኝነት የፖሊስ ለውጥ በማድረግ አሁን ላይ ተማሪዎች ስርዓት ይዘው በመፈተን ያጠኑትን፣ ያነበቡትንና የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ ከማስቻልም በላይ በዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ሰዎች ለፍተው ጥረው አንብበው የሚበቁበት ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ትውልዱ በእውቀቱና በችሎታው መድረስ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትውልድን መቅረፅ ለሀገር እድገትና ለፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት በተሻለ መልኩ የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች ለፈተና ሲጓዙ እንደሀገር ስጋትና ዜጋ ጨራሽ የሆነው የትራፊክ አደጋም የፈተና ስርዓቱን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የክልል የጸጥታ አካላት ፈተናውንም ሆነ ተፈታኝ ተማሪዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው እንዲያሽከረክሩ መደረግ አለበት ብለዋል። ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ባለፉት አመታት ከነበሩ ችግሮች በመነሳት በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ጥበቃ ፖሊስ በማቋቋም የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ማድረግ ተችሏል መባላቸውን ኢ.ፌ.ፖ.ሚ ዘግባል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡  (ሰኔ...

Comments