Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 17, 2025 at 07:58 AM
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል። (ሰኔ 10/2017 ዓ.ም) በክፍለ ከተማው መሰጠት የጀመረው የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በ17 የመፈተኛ ጣቢያዎች 3200 በላይ ተማሪዎችን ፈተናዉን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ፣ የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ፣ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ አስታጥቄ ፈተናዉን በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡ ተማሪዎች በጠዋቱ ፈረቃ አማርኛ ከሰሃት ላይ ደግሞ እንግሊዘኛ ፈተናዎችን የሚወስዱ ሲሆኑ ሌሎች ትምህርቶችንም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚወስዱ ይሆናል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 80,313 ተማሪዎች በ192 የፈተና ጣቢያዎች የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው እና በቂ ፈታኞች ፣ ጣቢያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸው ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል።  (ሰኔ...

Comments