Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 17, 2025 at 10:49 AM
የ2017 እቅድ አፈጻጸምና የ2018 የትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ውይይት በማድረግ ሪፖርቱንና እቅዱን አጽድቀዋል፡፡ (ሰኔ 10/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 እቅድ አፈጻጸምና በ2018 የትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ ላይ የቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄዳል፡፡ በውይይቱ የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ2017 ትምህርት ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸምና የ2018 ትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ እንዲሁም የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የ2017 በጀት አመት የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርትንና የ2018 በጀት አመት የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የሚከናወኑ የትምህርት ልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በ2017 የትምህርት ዘመን በርካታ ስራዎችን ለማከናወን የቻልን ሲሆን የተከናወኑ ተግባራትን ፣ የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን እንዲሁም በተግባር አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን በዝርዝር በመፈተሽ እንዲሁም የተመዘገቡትን አበረታች ውጤቶች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ጉድለቶችን ለይቶ በማስተካከል በቀጣይ በ2018 ትምህርት ዘመን ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ አራት ስትራቴጂክ ትኩረት መስኮች ላይ መሰረት በማድረግ የሚሰራ መሆኑን ጠቅሰው ሪፖርቱና እቅድ መጽደቁን ገልጸዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: የ2017 እቅድ አፈጻጸምና የ2018 የትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት...

Comments