Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 17, 2025 at 12:02 PM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የከሰዓቱን የፈተና አሰጣጥ በህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘትና ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡ (ሰኔ 10/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍለ ከተማ አቀፍ ፈተና ለ80,313 ተማሪዎች በ192 የፈተና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ከአቶ ዲናኦል ጫላ ጋር በመሆን የከሰዓቱን የፈተና አሰጣጥ በህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘትና ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡ በፈተና መስጫ ጣቢያው ከሰባት የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የመጡ 701 ተማሪዎች ፈተናዉን በመውሰድ ላይ የሚገኙ መሆኑን ከጣቢያ ሀላፊዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የከሰዓቱን የፈተና አሰጣጥ በህዝባዊ ...

Comments