Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 18, 2025 at 06:27 AM
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ ዓቀፍ ፈተና ለሁለተኛ ቀን በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል። (ሰኔ 11/2017 ዓ.ም) በትላንትናው እለት መሰጠት የጀመረው የ2017 ዓ.ም 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በክፍለ ከተማው በ20 የፈተና ማዕከላት በ85 ትምህርት ተቋማት 11,580 ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 በሚገኘው በየካ አባዶ እና ጎዴ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው የሁለተኛ ቀን ፈተና ማስጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የቢሮ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ፣ የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሌሊስቱ ተስፋዬ ተገኝተው ተማሪዎችን አበረታተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፈተናው በተያዘለት መርሀ ግብር መሰረት ለሁለተኛ ቀን በጥሩ ሁኔታ በመሰጠት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 10 እስከ 12 ድረስ እንደሚሰጥ ቀደም ሲል መገለፁ ይታወቃል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ ዓቀፍ ፈተና ለሁለተኛ ቀን በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ...

Comments