Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 18, 2025 at 10:01 AM
የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተና አሰጣጥ ተገመገመ፡፡ (ሰኔ 11/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፉ ፈተና መሰጠት የጀመረ ሲሆን የፈተናዉን አሰጣጥ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የክፍል ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ሂደቱን የሚከታተል የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ከማዋቀር ጀምሮ በቂ የፈተና አስፈጻሚዎችን በመመልመል ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸው የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ፈተናው በስኬት እንዲሰጥ እያደረጉት ያለዉን ጥረት አድንቀው ፈተናዉ በውጤታማነት እንዲሰጥ በቀጣይ ቀንም በልዩ ትኩረት መስራት እንዲሚገባ ተናግረዋል፡፡ ለሁለተኛ ቀን በመሰጠት ላይ የሚገኘው ፈተና በሁሉም ጣቢያዎች ያለምንም ችግር እየተሰጠ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዉ የጣቢያ ሀላፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲሁም ፈታኝ መምህራን ፈተናው በተቀመጠለት እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተና አሰጣጥ ተገመገመ፡፡  (ሰኔ 11/2017 ዓ.ም)  በአዲስ ...
👍 1

Comments