Addis Ababa Education Bureau
June 19, 2025 at 06:28 AM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የ2017 ዓ.ም አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተካሄዱ የፋይዳ ዳሰሳ ጥናቶችን ገመገሙ።
(ሰኔ 12/2017 ዓ.ም) የፋይዳ ዳሰሳ ጥናቶች ከቢሮው በተውጣጡ ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎች በበጀት አመቱ በመሪ እቅድ እንዲሁም የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ በአጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች የተገኙ ውጤቶችን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን በመርሀግብሩ ጥናቶቹ ቀርበው በስትራቴጂክ ካውንስል አባላቱ ተገምግመዋል።
የፋይዳ ዳሰሳ ጥናቶቹ በ2017 ዓ.ም ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ ተግባራት ያመጡትን ውጤት በመገምገም ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተሻለ ስራ ለመስራት እንደመካሄዳቸው በቀጣይ የጥናቶቹን ግኝቶች እና ምክረ ሀሳቦች መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስገንዝበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc