Addis Ababa Education Bureau
June 19, 2025 at 07:42 AM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የሶሰተኛ ቀን የፈተና አሰጣጥን በህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘትና ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡
(ሰኔ 12/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍለ ከተማ አቀፍ ፈተና ለ80,313 ተማሪዎች በ192 የፈተና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ ጋር በመሆን የሶሰተኛ ቀን የፈተና አሰጣጥን በህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘትና ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡
በፈተና መስጫ ጣቢያው ከሰባት የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የመጡ 701 ተማሪዎች ፈተናዉን በመውሰድ ላይ የሚገኙ መሆኑን ከጣቢያ ሀላፊዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc