Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
June 19, 2025 at 11:46 AM
ላለፉት ሶስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገለፀ። (ሰኔ 12/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 192 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለሞ ሙላቱ ገልፀዋል። ሀላፊው በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈተናቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ፈተናው በጭር ጊዜ ውስጥ ታርም ይፋ ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የተመደቡ የጸጥታ አካላ ፣ ፈታኞች ፣ የጣቢያ ኃላፊዎች ፣ ሱፐርቫይዘሮችና የፈተና አስፈጻሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በትጋት በመወጣታቸው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለማግኘት https://linktr.ee/aacaebc
Image from Addis Ababa Education Bureau: ላለፉት ሶስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው  የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገለፀ። ...

Comments