Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
June 21, 2025 at 06:31 AM
ምክትል የሚሲዮኑ መሪ በተገኙበት ከትግራይ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ተደረገ፤ (ሰኔ 14/2017 ዓ.ም) ምክትል የሚሲዮኑ መሪ ክቡር ከበደ አበራ በተገኙበት ከኢትዮጵያ የትግራይ ልማት ማህበር ጽ/ቤት አመራሮች እና በጅቡቲ ከትግራይ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ተደርጓል። ክቡር ከበደ አበራ በመክፈቻ ንግግራቸው ሚሲዮኑ የልማት ማህበሩን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህም በዚህ አደረጃጀት ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማበረታታት ያለመ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። የማህበሩ አመራሮች በበኩላቸው እስከአሁን ኤምባሲው ማህበሩ እንዲጠናከር እያደረገ ላለው ድጋፍ እና ክትትል በማመስገን፣ የልማት ማህበሩ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ፣ በቀጣይ ከንዑስ ልማት ማህበራት ጋር ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች እና የዳያስፖራ አባላት መጨመር ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በመጨረሻም የጂቡቲ ቅርንጫፍ ማህበር ከዋናው ጽ/ቤት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በቀጣይ የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት መክረዋል።
Image from Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ: ምክትል የሚሲዮኑ መሪ በተገኙበት ከትግራይ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ተደረገ፤  (ሰኔ ...

Comments