ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 12, 2025 at 12:02 PM
ሰኔ 5 2017 ወደ እንግሊዝ ለንደን ለማምራት የተነሳ የህንድ የመንገዶች አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡ 242 ሰዎችን ያሳፈረው አውሮፕላን የተከሰከሰው ከአህመድአባድ ኤርፖርት እንደተነሳ ወዲያውኑ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ ከባድ ጭስ እየተትጎለጎለ ነው ተብሏል፡፡ የወደቀው አውሮፕላን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር መሆኑ ታውቋል፡፡ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ቃጠሎው ለማጥፋት እየታገሉ ነው ተብሏል፡፡ ከአደጋው በሕይወት የተረፉ ሰዎች ስለመኖራቸው የተሰማ ነገር የለም፡፡ አደጋ የገጠመው አውሮፕላን የኤር ኢንዲያ አየር መንገድ ንብረት መሆኑ ታውቋል፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Image from ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1): ሰኔ 5 2017    ወደ እንግሊዝ ለንደን ለማምራት የተነሳ የህንድ የመንገዶች አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡  242 ...

Comments