
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 13, 2025 at 07:18 AM
ሰኔ 6 2017
የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ ከባድ ድብደባ ፈፅሜያለሁ አለ፡፡
ጦሩ ድብደባዬ በኢራን የኒኩሊየር ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ነው ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል አዛዥን ሁሴን ሰላምን ገድያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
ሌሎች የኢራን የጦር አዛዦችም በድብደባው መገደላቸው ታውቋል፡፡
የኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን፤ እስራኤል በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ በፈፀመችው ድብደባ ሕፃናትን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን ገድላብናለች ሲል ዘግቧል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ኢራን ለእስራኤል ሕልውና እጅግ አደገኛ ሀገር ነች ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
እስራኤል የአፀፋው ጥቃት ሊሰነዘርባት እንደሚችል ገምታለች፡፡
በዚህም የተነሳ የአስቸኳይ ጊዜ ስራ ላይ ማዋሏ ታውቋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
