
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 13, 2025 at 07:34 AM
ሰኔ 6 2017
የገቢ ግብር አዋጅ ተሻሽሎ ረቂቅ ተሰናድቶለታል፡፡
ደመወዝተኛውን በተመለከተ ምን ያህል ደመወዝ ላይ፤ መንግስት ምን ያህል በመቶ ግብር ይቁረጥ የሚለው በረቂቁ ላይ አልሰፈረም፡፡
ለውይይትም ክፍት ሆኗል፡፡
ይሁንና ገንዘብ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባሰናዳው የውይይት መድረክ ላይ ግብር የማይቆረጥበት ዝቅተኛው የደመወዝ መጠን ከ2,000 ብር ጀምሮ ይሆናል የሚል አቋም እንዳለው ተናግሯል፡፡
ከ10,900 ብር ጀምሮም በነበረው 35 በመቶ ግብር እየከፈሉ እንደሚቀጥሉ መንግስት አቋሙን አሳውቋል፡፡
የዘርፉ ባለሙያዎች ግን ያለውንና በመጭው ጊዜይም እየባሰ ይመጣል ያሉትን የመግዛት አቅም መዳከም አንስተው ማሻሻያው እንደገና ይታይ እያሉ ነው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/y2jabs49
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il