
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 13, 2025 at 09:09 AM
ሰኔ 6 2017
ለመጪው በጀት ዓመት ለክልሎች መደገፊያ ከተያዘው በጀት ከፍተኛውን የሚይዘው ኦሮሚያ ሲሆን ከ108.4 ቢሊየን ብር በላይ ተመድቦለታል፡፡
#አዲስ_አበባ በረቂቅ በጀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በጀት ሳይደለደልላት ቀርቷል፡፡
የፌዴራል መንግስቱ ለክልሎች መደገፊያ ከያዘው በጀት በሁለተኛ ደረጃ የአማራ ክልል ድርሻውን የሚይዝ ሲሆን 67.9 ቢሊየን ብር ተደልድሎለታል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ሶማሌ ክልል 31.4 ቢሊየን ብር እንዲሁም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ22 ቢሊየን ብር 4ኛውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ትግራይ ክልል 18.9 ቢሊየን ብር እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 18.5 ቢሊየን ብር በጀት የተያዘላቸው ናቸው፡፡
ሲዳማ ክልል 12.9 ቢሊየን ብር፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና አፋር ክልል ተቀራራቢ ከ9.5 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው ናቸው፡፡
ቀሪዎቹ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በስተቀር ማለትም ሐረሪ፣ ጋምቤላ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከ5 ቢሊየን ብር በታች የተመደበላቸው መሆኑ ከረቂቅ በጀቱ ተመልክተናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከከዚህ ቀደሙ በተለየ ሁኔታ በዚህ አመት በረቂቅ በጀቱ አልተካተችም፤ ምክንያቱ ምን እንደሆነም በረቂቅ በጀቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

👍
1