ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 13, 2025 at 01:01 PM
ሰኔ 6 2017 ለተቀጣሪ ሠራተኞች የላይኛው ጣሪያ ተብሎ የሚከፈለው 10,900 ብር ደመወዝ አሁን ባለው የኑሮ ሁኔታ፣ የዝቅተኛው ሰራተኛ መነሻ ክፍያ መሆን ነበረበት ተባለ። ግብራቸውን በአግባቡ የማይከፍሉ ብዙ በመሆናቸውና የግብር አሰባሰቡም ዝቅተኛ በመሆኑ መንግስት በሚፈልገው ልክ በሠራተኛ የገቢ ግብር ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ይቸገራል ተብሏል። ለዘጠኝ ዓመት የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ይተካል ተብሎ በተሰናዳው ረቂቅ መሠረት፤ ከግብር ነፃ የሚደረግ የሰራተኛ ደመወዝ አሁን ካለበት 600 ብር ወደ 2000 ብር ከፍ እንዲል ታስቧል። በኢትዮጵያ የሚሰበሰበው #የገቢ_ግብር ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ ድርሻው 6.8 በመቶ ብቻ መሆኑን ያነሱት በገንዘብ ሚኒስቴር የታክሲ ፖሊሲ መምሪያ ሀላፊው አቶ ሙላይ ወልዱ፣ ይህንን ማሻሻያ ማድረግ ብቻውን የሚሰበሰበው ግብር በቢሊየን ብር እንዲቀንስ ያደርጋል ብለዋል። አሁን ባለው ሁኔታ ትልቅ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ይቸገራል ሲሉ ተናግረዋል። የገቢ ግብር አዋጁ ረቂቅ ለውይይት በቀረበበት ዝግጅት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የውጭ እና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው አቶ አያሌው አህመድ፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራውን ሰራተኛ እያገኘ ያለውን አነስተኛ ክፍያ አንስተዋል። ኢኮኖሚውን እያንቀሳቀሰ ያለው ሰራተኛ እየተከፈለው ያለው ደመወዝ በወር ከ1300 ያለበለጠ እንደሆነ አንስተው ይህ ወደ ዶላር ሲቀየር በወር 7 ዶላር ከ50 ሳንቲም ብቻ ነው ብለዋል። እነዚህ ሰዎች በአንድ በኩል ልጆቻችን ናቸው በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው ብለዋል። ይህ የፋብሪካ ተቀጣሪ ሰራተኛ ቤተሰቡን እንኳን በአግባቡ መመገብ ባይችል እሱ እንኳን በልቶ ስራ ቦታ መምጣት መቻል አለበት ሲሉ ተናግረዋል። ከፍተኛው 35 በመቶ ግብር የሚከፈልበት የ10,900 ብር ወርሃዊ ደመወዝም አሁን ባለው የኑሮ ሁኔታ ዝቅተኛው ክፍያ መሆን ነበረበት ብለዋል። ይህ ደመወዝ ተጨማሪ 7 በመቶ ግብር ሲቆረጥ የሚቀረው 48 በመቶው ገንዘብ ብቻ መሆኑን አንስተው ከሱም ላይ እቃ ሲሸምት ገንዘቡን በቫትና በሌላውም ያጣዋል ሲሉ ተናግረዋል። ቢያንስ እነዚህ ወጪዎች ታስበው ለሰራተኛው ቢመለስለት ሲሉ ጠይቀዋል። ይህ ለተቀጣሪው ሰራተኛ ድህነቱን የሚያጣድፍ እና የሚያከፋ ሆኖበታል ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈም የውሎ አበልና፣ የስራ ማበረታቻ ሽልማት እንዲሁም ዓመታዊ ጉርሻም ሳይቀር ታክስ እንዲከፈልበት መሆኑም ተገቢ አለመሆኑን አንስተዋል። የሚሻሻለው አዋጅም ይህንን ሁሉ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት ብለዋል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/hfrt/ ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
👍 1

Comments