ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 13, 2025 at 04:46 PM
#የቅዳሜ_ጨዋታ የነገ ሰኔ 7 2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡ ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በ #ማሟሻ ይጀመራል፡፡ ማሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ ነበሩት #ይስሃቅ_ራቢና እየነገረ ያቆየናል፡፡ ተፈሪ አለሙ በትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ ስለ ዕውቁ ባለቅኔ፣ ገጣሚና ሃያሲ #ዮሐንስ_አድማሱ (ክፍል 2) ያወሰናል፡፡ የቅዳሜ ጨዋታ የእንግዳ ሰዓታችን፤ ለረጅም ዓመታት ኑሯቸውን በአሜሪካ የመሰረቱት ፓስተር #ሀንፍሬ_አሊጋዝ ከመዓዛ ብሩ ጋር የሚያደረጉት ጨዋታ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ሲል ይጀምራል፡፡ ድራማ እንዲሁም ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡ ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ! የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments