ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 17, 2025 at 11:12 AM
ሰኔ 10 2017 የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት የፈፀሙ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚቀጡበት መመሪያ ስራ ላይ ዋለ፡፡ በተሻሻለው መመሪያ መሰረት የሀይል ስርቆት የፈፀመ መኖሪያ ቤት ወይም ግለሰብ 20,000 ብር ይቀጣል ተባለ። የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ለሚፈፅሙት የሀይል ስርቆት ደግሞ 1 ሚሊየን ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ። በበጀት ዓመቱ 11 ወራትም 298 ደንበኞቹ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት መፈፀማቸውን አገልግሎቱ እወቁልኝ ብሏል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲሰላ 259 ሚሊየን ብር ኪሳራ እንዲደርስብኝ አድርጓል ብሏል። ከዚህ ቀደም የሀይልም ሆነ የመሰረተ ልማት ስርቆት የሚፈፅሙ ደንበኞችን የሚቀጣ የህግ ማእቀፍ ቢኖርም ዝርዝር የማስፈፀሚያ ደንብ እና መመሪያ አለመኖሩ ለመሰረተ ልማቶቹ የሚደረግ ጥበቃ ክፍተት እንዲኖረው አድርጓል። በተጨማሪም ወንጀለኞቹ ላይ አስተማሪ ቅጣት ሲጣልባቸው አለመታየቱ ችግሩ እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንያች መካከል መሆኑን የተናገረው አገልግሎቱ በዚህም ምክንያት የሀይል ስርቆትን የፈፀሙ ደንበኞች ሲዳኙበት የነበረው ህግ መከለሱን እና ወደ ስራ መግባቱን ተናግሯል። በዚህም አገልግሎቱ ፈትኖኛል ያለውን የሀይል ስርቆት ለመቀነስ ተሻሽሏል ባለው መመሪያ መሰረት የሀይል ስርቆት ፈፅሞ የተገኘ የንግድ ቤት 500 ሺህ ብር፣ የዝቅተኛ ኢንዱስትሪ 750 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል ተብሏል። የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ለሚፈፅሙት የሀይል ስርቆት 1 ሚሊየን ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የተነገረ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት ደግሞ 20 ሺህ ብር ተጥሏል ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት። ደንበኞች ከዚህ ቅጣት በኋላ በድጋሜ የሀይል ስርቆት የሚፈፅሙ ከሆነ ደግሞ የመጀመሪያ ቅጣታቸውን በእጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋል መባሉን ሰምተናል። ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments