
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 18, 2025 at 01:15 PM
ሰኔ 11 2017
አዲስ አበባ ህንፃዎቿም፣ መኖሪያ ቤት አጥሮቿም ንግድ ቤቶቿም ተመሳሳይ ቀለም ተቀብተዋል፤ እየተቀቡም ነው፡፡
ይህም ህንፃን ከህንፃ ለመለየት እንኳን አስቸጋሪ ሲያደርገው ይታያል። አሰራሩ ወደ ሌሎች ከተሞችም እየተዛመተ ነው፡፡
ይህንን የቀለም ቅብ ጉዳይ እንዴት ይታያል ስንል የዘርፉ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡
ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የቀለም ቅብ ሳይንስ ባለሞያ ናቸው። እሳቸውም ከሌሎች ያደጉ ሃገራት ልምድ አንፃር ከተማን አንድ ወጥ ቀለም መቀባት በሞያው አይመከርም ይላሉ።
ባለሞያው በተለየ ምክንያት ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀትና በረሃማ የአየር ንብረት ውስጥ ያሉ ከተሞችን የሙቀት መጠን ለመቀነስ ካልሆነ በቀር እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞችን ተመሳሳይ ቀለም ማልበስ #ቀለም ከማህበረሰብ ጋር ያለውን የታሪክ፣ የስነ ልቦና እና የፍልስፍና መስተጋብር ሳይንሳዊ ትርጉም ይጣረሳል ይላሉ።
በከተማ የቀለም ቅብ ሳይንስ (Urban color planning) ህግ ስርዓት ያልጠበቀ ዥንጉርጉር የከተማ ቀለም ቅብና በተቃራኒው ደግሞ የአንድ አይነት ወጥ የቀለም ቅብ አይፈቀድም የሚሉት ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ሌሎች የክልል ከተሞች እንደ አዲስ አበባ ወጥ ቀለም ሳይሆን አከባቢያዊ የከተማ ቅብ ስርዓትን (zonal coloring system) እንዲጠቀሙ መክረዋል።
ባለሞያው አከባባያዊ የከተማ ቀለም ቅብ ስርዓት፤ በአንዲት ከተማ ውስጥ ያሉ ሰፈሮችን ታሪክ፣ የማህበረሰብ ስነልቦናና ፍልስፍና ማስረዳት ይችላል ነው የሚሉት።
ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/tgh5r/
ንጋት መኮንን
