ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 18, 2025 at 04:26 PM
ሰኔ 11 2017 ኢትዮጵያ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን መብት ለማስከበር የተለያዩ አለም አቀፍ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያ መቆየት የሚችሉት 6 ወር ብቻ እንደሆነ ኢትዮጵያ የተቀበለችው የካምፓላው ስምምነት ያስገድዳል፡፡ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ሲኖሩ የዕለት እርዳታ የማግኘትና ማንኛውንም ሰብአዊም ይሁን ዲሞክራሲያዊ መብታቸው መጠበቅ እንዳለበት ያዝዛል፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ ማፅደቋም ይታወሳል፡፡ አዋጁ ቢጸድቅም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ስላልወጣ ስለ አዋጁ ብዙ ማለት ባይቻልም፤ ተፈናቃዮችን መልሶ ከማቋቋም ጋር ተያይዞና ችግርንም በራስ አቅም ከመመለስ አኳያ መንግስት ሊተገብራቸው የሚችሉ ስራዎች በህጉ መደንገጋቸውን ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የህግ ባለሞያው ጥጋብ ደሳለኝ አስታውሰዋል:: ይህ በእንዲ እናዳለ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ህግ ቢኖርም አፈፃፀሙ ላይ ክፍተት በመኖሩ በትምህርት ገበታ ላይ መኖር የነበረባቸው ህፃናትና ከራሱ አልፎ ለሃገሬው ሰው የሚተርፈው ገበሬው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለዓመታት በመጠለያ እንዲቆይ ተደርጓል ሲሉ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ባልተስተካከሉበት ሁኔታ የካምፓላው ስምምነትም ይሁን የሀገር ውስጥ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ ቢወጣም ችግሮቹን እየተቻለ አይደለም ብለዋል የህግ ባለሙያው፡፡ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተፈናቃዮች በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በተለያዩ ክልሎች ተጠልለውና እርዳታ ጠባቂ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/gtyr/ ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments