ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 19, 2025 at 11:53 AM
ሰኔ 12 2017 ያልፍልኛል ነገዬ የተሻለ ይሆናል ብለው በህጋዊም ሆነ በህገ ወጥ መንገድ ባህር ተሻግረው ወደ አረብ ሀገራት እና ሌሎችም ሀገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡት ኢትዮጵያውያን ቀን ሌት ሳይሉ ተጉዘው፣ ባህር አቋርጠው እድል ከቀናቸው ያሰቡበት ቦታ ይደርሳሉ፡፡ እዚያ ከደረሱ በኋላም ግን ሁሉም ነገር እንዳሰቡት ሳይሆንላቸው ይቀርና ብዙ ፈተናዎችን ይጋፈጣሉ፡፡ ገሚሱ ሰውነቱ ላይ ጣል ያደረገውን ጨርቅ ብቻ ይዞ ባዶ እጁን ወደ ሀገሩ ይመለሳል፣ ገሚሱ ህይወቱን ያጣል፣ ከፊሉ ደግሞ የጤና መታወክ ያጋጥማቸው እና ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ በህጋዊ የሚሄዱትም ቢሆን እንደዚህ ዓይነት ችግሮች ሲያጋጥማቸው ማየት አልያም ደግሞ ረጅም ዓመታትን ሰርተው ምንም ዓይነት አንጡራ ሀብት ሳይኖራቸው ይመለሳሉ፡፡ መንግስትም ከስደት ተመላሽ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በሚያጋጥሟቸው ችግሮች ተመልሰው ለስደት እንዳይዳረጉ የስራ እድልን እየፈጠርኩላቸው ነው ሲልም ይሰማል፡፡ በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ የስራ እና ክህሎት ቢሮ በተሰጠኝ ሀላፊነት መሰረት ከስደት ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሰዎች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው እያደረኩ ነው ብሏል፡፡ ከስደት ተመላሾች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ከማድረግ ባለፈ የተሰዳጅ ቁጥርን እንዲቀንስ እየሰራሁ ነው ያለው ቢሮው ለዚህም በመደበኛ ፕሮግራም የስራ እድሎችን እያመቻቸ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/gfgfh/ ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments