ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 19, 2025 at 11:56 AM
ሰኔ 12 2017 የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፍወርቅ ተክሌን የስነ ጥበብ ስራዎች እና ሌሎች ንብረቶች ከተረከበ በኋላ ያስቀመጣቸው ለአቧራ ተጋላጭ በሆነ ቦታ መሆኑ ተነገር ፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በበኩሉ የኪነ ጥበብ ስራዎችን የሚያነፍስ ራሱን የቻለ ለቅርስ ጥበቃ ባለሙያ ቀጥሪያለሁ ይላል፡፡ ይህ የተነገረው የመንግስት ወጭ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በባለስልጣኑ የተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምዝገባ ጥበቃ እና እንክብካቤን የስራ አፈጻጸም በተመለከት የ2015/16 በጀት ዓመት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን መነሻ በማድረግ የተቋሙ የስራ ሀላፊዎች ላይ ምላሽ እንዲሰጡባቸው ጥያቄ ከቋሚ ኮሚቴው ቀርቦባቸዋል፡፡ ቅርሶች በአግባቡ ጥበቃ፣ ምዝገባ፣ ጥገና እና እንክብካቤን እየተደረገላቸው መሆኑን መከታተሉን በተመለከተ በተደረገ ኦዲት ሲደረግ ባለይዞታዎች እና ባለቤቶች ቅርሶችን እንዲሁም በራሱ ይዞታ ስር ያሉ ስብስቦች በአግባቡ እንክብካቤና ጥገና እያደረጉ ስለመሆኑ ለመከታተል የሚያስችል አሰራር ሳይዘረጋ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፍወርቅ ተክሌን የስነ ጥበብ ስራዎች እና ሌሎች ንብረቶች ከተረከበ በኋላ የምዝገባ ኮድ ተሰጥቷቸው ያልተመዘገቡ መሆኑን የኦዲት ግኝቱ ያሳያል፡፡ በባለስልጣኑ ህንፃ የታችኛው ወለል ላይ የአርቲስቱ ስራዎች ጽዳቱ ባልተጠበቀ እና ከፍተኛ ሽታ ባለው ክፍል ውስጥ መቀመጣቸውን በኦዲት መረጋገጡን የተናገረው ቋሚ ኮሚቴ ለምን ይህ እንደሆነ እና አሁንስ ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው ሲል ጠይቋል፡፡ ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የመስሪያ ቤቱ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፍወርቅ የስነ ጥበብ ስራዎች ወደ ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የመጡት የአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ሊታደስ ሲል የስራ ሀላፊዎቹን እንደነበር አስረድተዋል፡፡ የስነ ጥበብ ስራዎቹ ወደ ባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ከመጡ በኋላም አንድ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያ በቋሚነት ሌላ ስራ ትቶ የስዕል ስራዎቹን እንዲናፍስ እና እንዲጠብቅ ተመድቦ እየሰራ መሆኑን የስራ ሃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ አሁን ግን መኖሪያ ቤት ቪላ አልፋ እድሳቱ ሙሉ በሙሉ ስለተጠናቀቀ ቤቱ የሙዚዬም መስፈርት እንዲያሟላ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም ካሜራ ፣ የእሳት መከላከያ እና ሌሎችም መስፈርቶች ዘመናዊ በሆነ መልኩ እየተሰሩ ነው ያሉት የስራ ሃላፊዎች በቅርቡም በይፋ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተናነረዋል፡፡ የአርቲስቱ የጥበብ ስራዎች በእድሳት ወቅት ጉዳት እንዳይደርስባቸው በጊዜያዊነት ባለስልጣኑ መስሪያ ቤት እንዲያርፉ መደረጉን ያስታወሱት የባለስልጣኑ የስራ ሀላፊዎች በቅርቡ ግን ወደ ቀድሞ ቦታቸው ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/457457/ ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments