ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 19, 2025 at 12:23 PM
ሰኔ 12 2017 በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዪ የፀጥታ ችግሮች በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ስራ ላይ ተፅዕኖ እያሳደሩ ነው ተባለ። ለአብነትም በአማራ ክልል ካሉ አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች አንድ መቶ ሃምሳ አንዱ በፀጥታ ችግር ምክንያት በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተነግሯል። ክልሉ በአገር አቀፍ ደረጃ ካሉ 25,282 አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የ21 በመቶዎቹ መገኛ እንደሆነ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አስመልክቶ ባካሄደው ጣናት ዙሪያ ዛሬ በካፒታል ሆቴል ውይይት ተካሂዷል። ጥናቱ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ከገጠር ይልቅ በብዛት በከተሞች እንደሚገኙ አሳይቷል ። ኢንዱስትሪዎቹ ከድጋፍ እና ማበረታቻዎች ጋር የተገናኙ የተለያዩ ችግሮች እንዳሉባቸው ተነግሯል ። ከቴክኒክና ሞያ ተቋማት ተመርቀው ዘርፉን የሚቀላቀሉ ተቀጣሪዎች የብቃት ጉዳይም ጥያቄ የሚነሳበት እንደሆነ የጥናቱ አቅራቢዎች ተናግረዋል። የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በአማራ፣ ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተሞች በሚገኙ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ጥናቱን እንዳካሄደ ሠምተናል። እነዚህ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በኢትዮጵያ ካሉ አነስተኛእና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች 71 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዙ ናቸው ተብሏል። በአገር አቀፍ ደረጃ ካሉ አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የ25 በመቶዎቹ መገኛ የሆነው ትግራይ ክልል ግን በጥናቱ አልተካተተም። ትግራይ ያልተካተተው ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት በክልሉ የፀጥታ ችግር ስለነበር ነው ተብሏል። ንጋቱ ረጋሳ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments