
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 19, 2025 at 04:15 PM
ሰኔ 12 2017
በግብዓት እጥረት ምክንያት የሀገር ውስጥ የምግብ ዘይት አምራቾች ከአቅማቸው በታች እያመረቱ መሆኑ ተነገረ፡፡
የዘይት አምራቾቹ የሚያስፈልጓቸውን የቅባት እህሎች በበቂ ሁኔታ ገበያ ላይ አለማግኘታቸው ስራቸውን እያስተጓጎለባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪ ማህበር ተናግሯል፡፡
የቅባት እህሎች በብዛት እሴት ሳይጨመርባቸው ወደ ውጭ ሀገር መላክ ላይ ትኩረት በማድረጋችን ምክንያት የሀገር ውስጥ ዘይት አምራቾችን ግብአት እያሳጣቸው ነው ያለው ማህበሩ በዚህ ምክንያት ደግሞ በሀገር ውስጥ የምግብ ዘይትን ለማምረት ብዙ ካፒታል ፈሰስ አድርገው፤ ሰራተኞችን ቀጥረው የሚያሰሩ ኢንዱስትሪዎችን ኪሳራ ውስጥ እያስገባቸው ነው ብሏል፡፡
በሌላ በኩል የቅባት እህሎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ አለመሆናቸው ደግሞ ሌላው የግብዓት እጥረት እንዲገጥመን ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል የተባለ ሲሆን ይህ መሆኑ ደግሞ ምርቶቹ ወደ ገበያ ሲወጡ ዋጋቸው እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡
የሀገር ውስጥ የምግብ ዘይት ዋጋቸው ከፍ ባለም ቁጥር ምርቶቹ ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ ይሄዳል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/rf/
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il