
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 20, 2025 at 05:18 PM
ሰኔ 13 2017
በተለያዩ ምድቦች በአለም አቀፍ መስፈርት መሰረት በየሀገሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በመምረጥ የሚሸልመው ቤስት ስኩል ፕራይዝ (Best School Prize 2025) ፤ የገላን ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከአስር እጩዎች መካከል አንዱ ማድረጉን ተናገረ፡፡
በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ከተወዳደሩ ከ3,200 ከሚበልጡና በመላው ዓለም ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ከ10 ምርጥ እጩዎች አንዱ የገላን ቁጥር ሁለት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሆኑ ተሰምቷል።
ትምህርት ቤቱ በቅጥር ጊቢ ውስጥ ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እንዲሁም ለወላጆች የሚመገቡትን የጓሮ አትክልትና ጤፍ ጭምር አምርቶ እራሱን በመቻሉ ለምርጫ መብቃቱ ተሰምቷል፡፡
ለ2025 ሽልማት በbest school prize አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ከ10 እጩዎች አንዱ በመሆን የተመረጠው ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ ኦልያድ ዋቅጋሪ እንዴት ከተቋሙ ጋር እንደተገናኙ ነግረውናል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዮሀንስ ወጋሶ(ዶ/ር) የገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሀገሪቱን የመማር ማስተማር ካሪኩለምን ተከትሎ ባለው ባዶ ቦታ የሰራው ስራ ለእጩነት አብቅቶታል በሀገር አቀፍ ደረጃም ተምሳሌት ሆኗል ይላሉ፡፡
ትምህርት ቤቶች በአራት ማዕዘን ተማሪዎችን ሰብስበው ከመምህሩ የሚነገረም ብቻ ሰምተው የሚመለሱበት ቦታ ሳይሆን የመማሪያ መስክ እንዲሁም የማህበረሰቡ የመለወጫ ማዕከል መሆን አለባቸው የሚለውን የመንግስት አሰራር ጭምር የገላን ቁጥር ሁለት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሟላ ተቋም ሆኗልም ሲሉ ዮሃንስ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በእድሜያቸው ትምህርት ቤት ባለመግባት ከእኩዮቻቸው እኩል መማር ያልቻሉ ተማሪዎችን በፈጣን የትምህርት ስርዓት በማስተማር በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ያገኘው ጄኔቫ ግሎባል የገላን ቁጥር 2 ትምህርት ቤትም እንዴት ለአለም አቀፉ ተቋም እንዳስተዋወቀው የጄኔቫ ግሎባል በኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር አቶ አበባው አብጤ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ላይ ከአፍሪካ በብቸኝነት ከአስሩ እጩዎች አንዱ ሆኖ የተመረጠው የገላን ቁጥር ሁለት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚፎካከረው ከፈረንሳይ፣ ከህድን፣ ከቱርክ፣ ከኮሎምብያ፣ ከቺሊ፣ ከኮሶቮ፣ ከኔፓል፣ ከዱባይ፣ እንዲሁም ለፔሩ ተወዳዳሪዎች ጋር መሆኑንም ሰምተናል፡፡
የ2025 የወርልድ best school prize አዋርድ ተሸላሚ የሆኑ ሀገር እንዲያስጠራ ባሉት 20 ቀናት ላይ በዚህ ( https://shorturl.at/mM5pf )
ማስፈንጠሪያ በመግባት ለገላን ቁጥር ሁለት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድምፃችሁን ስጡ ሲሉም ኃላፊዎቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/t79/
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il