
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
June 20, 2025 at 05:27 PM
#የቅዳሜ_ጨዋታ
የነገ ሰኔ 14 ቀን 2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡
ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡
ሟሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ #የእስራኤልና_የኢራን ጦርነት መነሻና አሁናዊ ሁኔታው እየነገረ ያቆየናል፡፡
ተፈሪ አለሙ በትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ የ50ኛ ዓመት ሙት አመቱን ምክንያት በማድረግ ስለ ዕውቁ ባለቅኔ፣ ገጣሚና ሃያሲ #ዮሐንስ_አድማሱ (ክፍል 3) ያወሳናል፡፡
በቅዳሜ ጨዋታ የእንግዳ ሰዓታችን፤ ለረጅም ዓመታት ኑሮቸውን በአሜሪካ የመሰረቱት ፓስተር #ሀንፍሬ_አሊጋዝ ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ (ሁለተኛው ሳምንት) ከቀኑ 9:00 ሰዓት ሲሆን ይጀምራል፡፡
ድራማ እና ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡
ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!
