
ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
May 29, 2025 at 03:26 AM
❗የኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉ዕርገት ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት አንዱ ቢሆንም በምዕመናን ዘንድ ግን እምብዛም አይታወቅም፡፡
🔴👉 በዓሉ የሚውለው በዕለተ ሐሙስ ነው ። ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት መውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሰረት የዘንድሮ በዓለ ዕርገት ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡
🔴👉 ዕርገት ማለት በግእዝ ቋንቋ "ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት" ማለት ነው።
🔵👉 ይኸውም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውል ዐቢይ በዓል ነው።
🔷👉 ጌታችን ከሙታን ተነሥቶ ከማረጉ በፊት በግልጽም በስውርም ምሥጢራትን ፣ ሕግጋተ ቤተክርስቲያንንና መጽሐፈ ኪዳንን ለሐዋርያትና ለቅዱሳን አንስት ሲያስተምር ቆየ። በዐርባኛውም ቀን ከፍ ከፍ እያለ ወደ ሰማይ ዐረገ።
🔴👉 በቤተክርስቲያናችን በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ በሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
🔷👉 ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከውም ምስባክም "ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐረገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል" የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲሆን ትርጉሙም "በምስራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ ፤ የኀይል የሆነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል።" ማለት ነው። (መዝ. ፷፯፥፴፫ /67፥33/)
🔴👉 የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት የተፈፀመው ስለ ምጽአቱ ባስተማረበት እና ዳግም ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት የደብረ ዘይት ተራራ ነበር። ቅዱስ ሊቃስ ይህንንም እንዲህ ሲል አስቀምጦታል፤ "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።" ( ሉቃ. ፳፬፥፶-፶፩)
🔷👉 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ለ40 ቀናት ያህል ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምራቸው ቆይቷል ።
🔷👉 "ደግሞ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለእግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው " ሲል ቅዱስ ሉቃስ እንደገለጸው ከትንሣኤው በኋላ በምድር ላይ የቆየው ለዐርባ ቀናት ብቻ ነው ። ከዐርባ ቀናት በኋላ በክብር በይባቤ ወደ ሰማይ ዐርጓል።
🔷👉 " ....ይኽን ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው" እንዲል ። (ሐዋ 1፥1-9 ) ጌታችን ያደረገውን /ዕርገቱንም/ ከደብረ ዘይት ተራራ ነው ። (ሉቃ 24-50-53)
🔴👉 ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ሲያስተምር "እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል ?" በማለት እንደገለጸው ዕርገቱ ፣ ክብሩ በሚገለጽበት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ለመቀመጥ ነው ። (ዮሐ 6፥62)
🔷👉 ይኽን ቅዱስ እስጢፍኖስ በዐይነ ሥጋው ለመመልክት መብቃቱን "እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ " በማለት ገልጾታል ። (ሐዋ 7፥57 )
🔵👉 ይኽን ጉዳይ አስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲህ በሰማያት ስላለን ፣ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ " ብሎአል ። (ዕብ 4፥14 7፥26 ) ስለጌታችን አምላክነት ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ባስረዳበት አንቀጽ "......በሥጋ የተገለጠ ፣ በመንፈስ የጸደቀ ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ ፣ በዓለም የታመነ ፣ በክብር ያረገ "ሲል ገልጾታል ። (1ኛ ጢሞ 3፥16 )
❗በክብር ያረገ አምላክ ከትንሣኤ ሙታን በኋላ ያለውን ዕርገታችንን የክብር ያድርግልን። በበረቱ ያቆየን።❗
#ፎሎው ማድረግ እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ግንቦት 21/2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube
🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16
❤️
👍
🙏
4