ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
May 31, 2025 at 05:08 AM
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ❗ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, 🔴👉 #ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብርህ ሐረገ ወይን #ፀሐይ "ማለት ነው። ሊቀ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 22 ቀን በ 277ዓ/ም ተወለደ ሃገሩ ፍልስጤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይበላል። አባቱ አንስጣስዮስ ይባላል። ከልዳ መኻንንት ተሹሞ ይኖር ነበር፥እናቱ ቴዎብስታ (አቅሌስያ ትባላለች።ማርታና እስያ እህቶች ነበሩት። 🔵👉 #10አመት ሲሞላው አባቱ ስለ ሞተ ሌላ ደግ ክርስትያናዊ መስፍን ከቤቱ አሳደገው። በጦር ሃይልም አሰለጠነው። 20 ዓመት ሲሞላው የ 15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቤሩት ሄደ። 🔴👉 በቤሩት ጣዖትን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል። 🔷👉 #ወደፍርስ ቢመለ ዱድያኖስ ሰባ ነገስታትን እና ጣኦታት ሰብስቦ ሲሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖት ቀናዒ ነውና ከቤተ መንግስቱ ገብቶ እኔ ክርስቲያን ነኝ በእየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ አለው። 🔶👉 እርሱንም ማንነቱን ከተረዳ በኃላ አንተ እማ የእኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ አለው።ቅዱስ ጊዮርጊስም ሹመት ሽልማትክ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ እየሱስ ክርስቶስ አልክድም አለ"። ❗👉 በዚ ግዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት እርሱ ግን"ይህን ከሀዲ እስከማሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ"በማለት እግዚአብሔርን ለመነና እንደ ጸሎቱ በእምነቱ ጽናት የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይቻለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው።❗ ❗የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ ረድኤቱ ጥበቃው ሁሉ አይለየን ❗ #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ ፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨ ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።። ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።። ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም ግንቦት 23/2017 ዓ.ም ሆለታ ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ 🔴👉 በቴሌግራም | Telegram 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom 🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp 👇👇👇👇👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w 🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube 👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@yonastube 🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube 👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@yonasmedia16
❤️ 1

Comments