ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
June 8, 2025 at 08:19 PM
❗#የ2017 #ፆመ_ሐዋርያት (#ሰኔ_ፆም)❗
#መቼ_ይገባል? #ለምንስ_ይፆማል??
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።
🔴👉 ይህ ፆም የሐዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኃላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።
🔷👉 የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል በዚህም መሠረት የዘንድሮው የ2017 ዓ.ም ሰኔ ፆም ሰኔ 2 ይገባል (ይጀምራል) ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል። የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
🔴👉 የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሐዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት ዕለት ነው ።
🔴👉 ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳኑ አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡
🔷👉 ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡
🔵👉 ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16
🔴⏩ እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
🔴⏩ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን ለብርሐነ ትንሳኤው ያደረሰን አምላክ ለፆሙ በሠላም ያድርሰን!!!!
🔷👉አንብበው ጨርሰዋል? እንግዲያውስ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ሼር በማድረግ ወንጌን ያዳርሱ!!
።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ሰኔ 1 / 2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube
🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16
❤️
1