ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
June 13, 2025 at 04:07 AM
❗ #ቅድስት_አርሴማ_ማን_ናት ??❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 አርሴማ ማለት በወርቅ ልብሶች የተጎናፀፈችና የተሸለመች መልከ መልካም ውብ ማለት ነው።
🔷👉 አርሴማ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ተብሎ የተነገረውን የክርስቶስ ወንጌል ተከትላ ዘመድ አዝማዶቿን ትታ ጌታችንን የተከተለች ቅድስት ናት።
🔶👉 የሮምና የአርመንያ ገዥዎች የነበሩ ሁለት ከሀዲያን ነገሥታት ዲዮቅልጥያኖስና ድርጣድስን በሃይማኖቷ ፀንታ ድል ያደረገች
🔷👉 የሮም ወታደሮች የሚያደርሱባት መከራና ግፍ እስራትና ግርፋት ያልበገራት መላ ህይወታቸውን ለእሳትና ለስለት ከሠጡት ከ27 ቱ ቅዱሳት ደናግል መካከል አንዷ ሠማዕት ነች።
🔷👉የሠማዕቷ ምልጃና እና በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን❗
❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ሰኔ 6/2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
❤
😂
❤️
🕯
9