ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
June 14, 2025 at 04:09 AM
❗#ስላሴን_ለምን_ቅድስት_ስላሴ❗
#እንላለን?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር፡-
🔶👉 አንድም ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብሎ አይጠረጠሩም፡፡
🔵👉 አንድም ሴት በባህሪዋ ልጅን ታስገኛለች፣ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ፡፡
🔴👉 አንድም ሴት አዛኝ ናት፣ለታናሹም ሆነ ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፣ ይራራሉ፣ ምህረትን ይሰጣሉ፡፡
🔵👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ”ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንፃር
ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ የምህረት ወንዶች ሥላሴ" በማለት ያመሰጥራል፡፡
🔶👉 ስለእዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፣ ርህራሄያቸውና፣ ይቅር
ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡
አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፣ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያቢሎስ እጅ ተይዞ በሐጥያት እንዲታመሙ አይወዱም፣ አይፈቅዱም በመሆኑም “ቅድስት” ይባላሉ፡፡
🔴👉 አንድም ሴት የልጇን ነውር አትፀየፍም ልጄ ቆሽሿል፣ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም፣ ሥላሴም የሰውን በሐጥያት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንጻር ቅድስት እንላቸዋለን፡፡
🔴👉 አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እነደዛው ናቸው በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ፡፡ ስለእዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንፃር ቅድስት ይባላሉ፡፡
❗በዚህ ምክንያት ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን በፍቅር እንጠራለን፡፡❗
🔷የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት አይለየን🔷
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ሰኔ 7/2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube
🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16
👍
🙏
3