ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
June 20, 2025 at 05:12 AM
#ቅዱስ_ሩፋኤል.......❗ ................................................ 🔵👉 ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› እንዲል (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡ የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቍስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ ‹‹በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል (ሄኖክ ፲፥፲፫)፡፡ 🔴👉 ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዳለ ሄኖክ (ሄኖክ ፮፥፫)፡፡ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው፤ ላረገዙ ሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ 🔴👉 ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ (ኗ በማኅፀን እያለ (ች) ተሥዕሎተ መልክዕ (በሥላሴ አርአያ መልኩ /ኳ/ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው አይለያቸውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ 🔵👉 ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል (ጦቢት ፫፥፰-፲፯)፡፡ ❗የቅዱስ ሩፋኤል ምልጃ ጥበቃው አይለየን አሜን/3/❗     ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።      ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።      ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።        ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም          ሰኔ 13/2017 ዓ.ም                ሆለታ ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ 🔴👉 በቴሌግራም | Telegram        👇👇👇👇👇👇 https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom 🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp        👇👇👇👇👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w 🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube       👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@yonastube 🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube       👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@yonasmedia16

Comments