Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 13, 2025 at 03:29 PM
*ሃይንከን ኢትዮጵያ ከአዲስ ሜትር ታክሲ ጋር በመተባበር "በልክ" የተሰኘ መርሃ ግብር አስጀመረ* ሰኔ 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሃይንከን ኢትዮጵያ አዲስ ሜትር ታክሲን የትግበራ አጋር በማድረግ፤ አሽከርካሪዎች ከጠጡ በጭራሽ እንዳይነዱ ግንዛቤን የሚያስጨበጥ "በልክ፣ በአግባብ በኃላፊነት - አራዳ ከጠጣ የማይነዳ" የሚል ዘመቻውን ትናንት ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል፡፡ ድርጅቱ በመስቀል ፍላዎር አደባባይ ያስጀመረው ይህ መርሃ ግብር በ50 የአዲስ ሜትር ታክሲዎች ላይ መልዕክቱን በመለጠፍ ሲሆን፤ መልዕክቱ ምንም አይነት መጠጥን የሚያበረታታም ይሁን ማን መልዕክቱን እንዳስተላለፈው የሚገልጽ ምልክት የለውም። "ጠጥቶ ማሽከርከር የሚያስከትለውን አደጋ በመገንዘብ እንደ አንድ ኃላፊነት እንደሚሰማው ድርጅት ያስጀመርነው ይህ ዘመቻ በ50 ታክሲዎች ላይ መልዕክቱን በመለጠፍ ለ6 ወራት እንዲቆይ እናደርጋለን" ሲሉ የሃይንከን ኢትዮጵያ የሴስቴይነብሊቲ የውጭና መንግሥታዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ ተናግረዋል። ይህ መልዕክት ታክሲዎቹ ተዘዋውረው በሚሰሩበት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በቀን ከ2 ሚልዮን በላይ ሕዝብ ይመለከተዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡ ሃይንከን ኢትዮጵያ ከዚህም ጎን ለጎን አልኮል መጠጥን በኃላፊነት መጠቀም በሚለው ዘመቻው ሥር፤ እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች (No for Underage Drinking) "አልኮል አልቀምስም" የሚል ስልጠናም እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡ የሃይንከን ምንም አሻራ ሳይገኝ ስልጠናውን የሚሰጡለት መንግሥታዊ ያልሆኑ የትግበራ አጋሮቹ ሲሆኑ፤ መርሃ-ግብሩ እስከ አሁን በመላው አገሪቱ ባሉ 11 ዩኒቨርሲቲዎች መካሄዱ ተመላክቷል፡፡ የ "በልክ" መርሀ-ግብር የሃይንከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ባርት ዲ ኬኒንክ፣ የሴስቴይነብሊቲ የውጭና መንግስታዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ፣ የአዲስ ሜትር ታክሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ኃይሉ እና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተወካይ አቶ ኢሳ አሰፋ እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስ ተወካዮች በጋራ በመሆን አስጀምረውታል፡፡ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *ሃይንከን ኢትዮጵያ ከአዲስ ሜትር ታክሲ ጋር በመተባበር "በልክ" የተሰኘ መርሃ ግብር አስጀመረ*   ሰኔ 6/2...

Comments