Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 13, 2025 at 03:33 PM
*በ89 ካምፓሶቻቸው ስልጠና ሲሰጡ በነበሩ 57 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ* 👉 *ተቋማቱ በድጋሚ የእውቅና ፈቃድ መጠየቅ የሚችሉት ከ2 እና ከ4 ዓመታት በኋላ ነው ተብሏል* ሰኔ 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 57 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ89 ካምፓሶቻቸው እየሰጡት የነበረው ትምህርት እና ስልጠና በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የተቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት ባለማሟላቱ እርምጃ እንደተወሰደባቸው፤ የኢፌድሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢንያም ኤሮ፤ በተቋማቱ ላይ የተወሰደው እርምጃ የፈቃድ እድሳት እገዳና የትምህርት መስክ ስረዛ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ተቋማቱ ቅጣት የተጣለባቸው የመማር ማስተማር ሥራ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ፈቃድ ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሲወስዱ የገቡትን ውል ባለመፈጸማቸው እና የሥነ-ስርዓት ጥሰት ስለተገኘባቸው መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። አክለውም፤ ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ባለፉት ዓመታት ትምህርታቸውን በተቋማቱ ተከታትለው ያጠናቀቁ 97 ሺሕ 567 ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ እና የምዝገባ መስፈርቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መመርመራቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም "በፍተሻው ወቅት ሐሰተኛ ማስረጃዎች፣ የ12ኛ ወይም የ10ኛ ክፍል ውጤታቸው ከዓመቱ የመቁረጫ ነጥብ በታች የሆነ ተማሪዎች፣ የሲኦሲ ፈተና ማስረጃ ያላቀረቡ፣ ፈቃድ በጊዜ አለማደስ እና ሌሎችም ችግሮች ተገኝተዋል" ብለዋል፡፡ ተቋማቱ ለተዘጉባቸው የትምህርት ዘርፎች በድጋሚ የእውቅና ፈቃድ መጠየቅ የሚችሉት ከ2 እና ከ4 ዓመታት በኋላ ነው ተብሏል። በ2017 የትምህርት ዘመን 92 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ124 ካምፓሶቻቸው 36 ሺሕ 729 ተማሪዎችን እያስተማሩ መሆኑን መረጃ መላካቸውም ተገልጿል። በእመቤት ሲሳይ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *በ89 ካምፓሶቻቸው ስልጠና ሲሰጡ በነበሩ 57 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ*   👉...

Comments